ይህንን ትምህርት ወደ ሚከተለው ቋንቋ ተቶርግሟል
- português - Portuguese
- اردو - Urdu
- Ўзбек - Uzbek
- Deutsch - German
- Shqip - Albanian
- español - Spanish
- বাংলা - Bengali
- bosanski - Bosnian
- ไทย - Thai
- română - Romanian
- Kiswahili - Swahili
- svenska - Swedish
- Tiếng Việt - Vietnamese
- 한국어 - Korean
- മലയാളം - Malayalam
- हिन्दी - Hindi
- Hausa - Hausa
- ελληνικά - Greek
- Türkçe - Turkish
- 中文 - Chinese
- Bahasa Indonesia - Indonesian
- Wikang Tagalog - Tagalog
- Français - French
- English - English
- العربية - Arabic
- नेपाली - Nepali
- italiano - Italian
- অসমীয়া - Assamese
Full Description
አንዲት መልዕክት ብቻ!
ዶ/ር ናጂ ቢን ኢብራሂም አል‐ዐርፈጅ
መታሰቢያነቱ
በእውነትና በኢኽላስ ትክክለኛዋን እውነታ ለሚፈልጉ
እና አስተዋይ አዕምሮ ላላቸው ይሁን።
ቅድመ-ንባብ ጥያቄዎች:
1) ከዚች አንዲት መልዕክት የተፈለገው ነገር ምንድን ነው?
2) መፅሀፍ ቅዱስስ ስለሷ የሚለው ምን ይሆን?
3) ቁርአንስ ስለሷ የሚለን ይኖር ይሆን?
4) ከዚህ በኋላስ ስለሷ አስተያየትህ ምን ይሆን?
ወደ ጉዳዩ ስንገባ:
አደም ከተፈጠረ በኃላ በሰብአዊነት ታሪክ አንዲት መሰረታዊ መልዕክት ወደ ሰዎች ተላከች፤ ይህችን ተልዕኮ ለማስታወስና እነርሱን ወደቀጥተኛው መንገድ ለመምራት ብቸኛውና እውነተኛ የሆነው አምላክ እንደነ አደም፣ ኑሕ፣ ኢብራሂም፣ ሙሳ፣ ዒሳ እና ሙሐመድ (ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ያሉ ነቢያቶችና መልዕክተኞችን ላከ፤ መልዕክቷም እንዲህ ነች:
ትክክለኛው አምላክ አንድ ብቻ ነውና እርሱን አምልኩት።
ይህችን መልዕክት ለማድረስ ከላካቸው መካከልም:
ኑሕ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ስለሆነ እርሱን ብቻ አምልኩ።"
ኢብራሂም "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ስለሆነ እርሱን ብቻ አምልኩ።"
ሙሳ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ስለሆነ እርሱን ብቻ አምልኩ።"
ዒሳ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ስለሆነ እርሱን ብቻ አምልኩ።"
ሙሐመድ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ስለሆነ እርሱን ብቻ አምልኩ።"
አሏህ የቆራጥነት ባለቤት የሆኑ መልዕክተኞችንና ሌሎች የምናውቃቸውንም የማናውቃቸውንም ነቢያቶቹንና መልዕክተኞቹን በርካታ ጉዳዮችን እንዲፈፅሙ ልኳቸዋል። ከነዚህ ጉዳዮች መካከልም:
1) መለኮታዊ ወሕይን ተቀብለው ለህዝቦቻቸውና ለተከታዮቻቸው እንዲያደርሱ፤
2) ተውሒድንና አምልኮን ለአሏህ ማጥራትን እንዲያስተምሩ፤
3) ሰዎች ወደ አሏህ በሚያደርጉት ጉዞ ሊከተሏቸው ዘንድ መልካም አርአያነትን በተግባርም በንግግርም ለማነፅ፤
4) ተከታዮቻቸውን አሏህን ወደ መፍራት፣ ወደ ታዛዥነቱ እና ትእዛዛቱን ወደ መከተል ለማቅጣጨት፤
5) ለተከታዮቻቸው የሀይማኖቱን መመርያና መልካም ስነምግባርን ለማስተማር፤
6) አመፀኞችንና ጣኦት አምላኪ ሙሽሪኮችን እንዲሁም ሌሎችንም ለመምራት፤
7) ከሞት በኃላ የሚቀሰቀሱና በስራዎቻቸውም ተጠያቂ መሆናቸውን ለማድረስ፤ በአሏህ ብቸኝነት አምኖ መልካምን የሰራ ምንዳው ጀነት እንደሆነ በአሏህ አጋርቶ እርሱን ያመፀም መመለሻው እሳት መሆኑን ለማሳሰብ ነው።
እነዚህን ነቢያትና መልዕክተኞችን የፈጠራቸውና የላካቸው አንድ አምላክ ብቻ ነው። ፍጥረተ አለሙም ይሁን ፍጥረታቱ የአንዱን አምላክ የአሏህን ህልውናና ብቸኝነት የሚያረጋግጡ ናቸው። የፍጥረተ አለሙም ይሁን የሰውም፣ የእንሰሳውም የመርዛማ ነፍሳቱም ፈጣሪ አሏህ ነው። የሞትም ፈጣሪ፤ የጠፊዋ ህይወትም ይሁን የዘለአለማዊዋ ህይወትም ፈጣሪ እርሱ ነው።
አይሁዶች፣ ክርስትያኖችም ሙስሊሞችም ዘንድ የሚገኙ ቅዱሳን መፅሀፎች ባጠቃላይ የአሏህን ህልውናና ብቸኝነቱን ይመሰክራሉ።
እውነታን የሚፈልግ ተመራማሪ የአምላክነትን ፅንሰ ሀሳብ በመፅሀፍ ቅዱስና በተከበረው ቁርአን ውስጥ በሚገባ ካጠና ሌሎች አምላክ ተብዬዎች የማይገለፁባቸው የሆኑ እርሱ የሚለይባቸው መገለጫ ባህርያቱን ለይቶ ማወቅ ይችላል። ከነዚህም መካከል:
1) እውነተኛው አምላክ ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አይደለም።
2) ትክክለኛው አምላክ ተጋሪ የሌለው ብቸኛ፤ ከአንድ የበዛም አይደለም፤ ወላጅም ተወላጅም የለውም።
3) አሏህ ከፍጡራን እሳቤ የጠራ በመሆኑ በዱንያ ዓይኖች የማይደርሱበት ነው።
4) አሏህ ዘልአለማዊ በመሆኑ የማይሞትና በፍጡራኑ ላይም የማይሰርፅና የማይሰፍር ነው።
5) አሏህ ራሱን ቻይ የሁሉም መጠጊያ፤ ከፍጡራኑም የተብቃቃ ነው። ፍጡራኑም የሚያስፈልጉት አይደለም፤ አባትም ይሁን እናት ፣ የህይወት አጋርም ይሁን ልጅ የለውም። መብላትም ይሁን መጠጣት አልያም የማንም እገዛ የሚያስፈልገው አይደለም። ነገር ግን እርሱ የፈጠራቸው ፍጡራን ሁሉ እርሱ የሚያስፈልጋቸው ናቸው።
6) አሏህ ምንም ተጋሪም ይሁን አምሳያ በሌለው አኳኃን በታላቅነት፣ በምሉእነትና በውብ መገለጫዎቹ ብቸኛ ነው። እርሱን የሚመስልም አንዳችም የለም።
ማናቸውም "አምላክ" ተብዬዎች ሙግታቸው ውድቅ ለመሆኑ እነዚህን መለኪያዎችንና መገለጫዎችን (እንዲሁም ሌሎች አምላክ ብቻ የሚለይባቸውን መገለጫዎችን) ብቻ መመርኮዝ እንችላለን።
አሁን ከፍ ብለን ወደጠቀስነው አንዲቷ መልዕክት ተመልሰን ከመፅሀፍ ቅዱስም ከቁርአንም የአምላክን አንድነት የሚያጠነክሩ ጥቅሶችን እየጠቀስን እንማማር። ከዛ በፊት ግን ይህችን ሃሳብ ላጋራችሁ:
አንዳንድ ክርስትያኖች እየተደነቁ እንዲህ ሊሉ ይችላሉ: "አምላክ አንድ ነው፤ እኛም የምናምነው በአንዱ አምላክ ነው። ታዲያ ቁምነገሩ ምንድን ነው?!"
ይሁን እንጂ እኔ ራሴ ስለክርስትና ካደረግኩት የብዙ መፃህፍት ጥናትና ምርምር፣ ከክርስትያኖች ጋር ካደረግኩት በርከት ያለ ውይይት ተነስቼ የደረስኩበት እውነታ እነርሱ ዘንድ (አንዳንዶች እንደሚያስቡት) "አምላክ" ሲባል የሚከተሉትን ያጠቃልላል:
1) እ/ር አባት
2) እ/ር ወልድ (ልጅ)
3) እ/ር መንፈስ ቅዱስ
በጉዳዩ ላይ እውነታ ፈላጊን ተፈጥሯዊ ማመዛዘንና ጤናማ አመክንዮው ክርስትያኖችን እንዲህ እንዲጠይቅ ያደርገዋል:
ሶስት አምላኮች እንዳሉ የሚያመለክትን ገለፃ እየተጠቀማችሁ "አምላክ አንድ ነው" ስትሉ ምን ማለታችሁ ነው?
አምላክ አንድ ሆኖ በሶስቱ ሰረፀን (1 በ 3) ? ወይስ ሶስት ሆነው በአንዱ ላይ ሰረፁ (3 በ 1) ?
ከዛም ባሻገር እንደአንዳንድ ክርስትያኖች እምነት እነዚህ ሦስቱ "አማልክት" በሚከተለው መልኩ የተለያየ ማንነት፣ አምሳል፣ ሚና እና ተግባራት አሏቸው:
1) እ/ር አብ = ፈጣሪ
2) እ/ር ወልድ = አዳኝ
3) እ/ር መንፈስ ቅዱስ = አማካሪና (የሚያበረታ)
ኢየሱስን "የአምላክ ልጅ ነው" ፣ ወይም "አምላክ ነው" ወይም "የአምላክነት ድርሻ አለው" ብሎ ማለት ከብሉይ ኪዳንና ከአዲስ ኪዳን አስተምህሮ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጋጭ ነው፤ አምላክን በዚች አለም ላይ ማንም እንደማያየው ያስተምራሉና፡
" እናንተም ከቶ ድምፁን አልሰማችሁም፤ መልኩንም አላያችሁም፤"
(ዮሐንስ፡ 5፡ 37)
"አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤"
(ወደ ጢሞቲዎስ፡ 6፡ 16)
"ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም"
(ዘጸአት ፡ 33፡20)
ከነዚህና መሰል አንቀፆች በመነሳት በሙሉ ቅንነት እውነቱን ለመናገር የሚጭርብኝ የግርምት ጥያቄ አለ፡ "ኢየሱስ አምላክ ነው" በሚል አስተምህሮ እና አምላክን ያየም ይሁን ድምፁን የሰማ አንድም እንደሌለ በሚያስተምሩ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አንቀፆች እንዴት ማስማማት ይቻላል?
ያኔ አይሁዶችና የዒሳ ቤተሰቦች መሲሑ ዒሳን (እንደአንዳንዶቹ አገላለፅ ደሞ እ/ር ወልድን) አላዩትም ነበርን? ድምፁንስ አልሰሙምን?
አምላክን ማንም እንዳላየውና ድምፁንም ማንም እንዳልሰማ በኦሪትና በወንጌል አስተምህሮ ተረጋግጦ የፀና አስተምህሮ ሆኖ ሳለ አይናቸው እያየ ድምፁንም እየሰሙት አብሯቸው የነበረው ዒሳ "አምላክ" ወይም "የአምላክ ልጅ" እንዴት ይባላል? እንደው የአምላክን እውነታ በተመለከተ የተደበቀ ሚስጥር ይኖር ይሆን?
የኦሪት አስተምህሮ ግን በተቃራኒው ነው። አምላክ እንዲህ ማለቱን ነውና የሚያስተምረው፡ "እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም። በስውር ወይም በጨለማ ምድር ስፍራ አልተናገርሁም፤ እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን እናገራለሁ ቅንንም አወራለሁ።" (ኢሳያስ፡ 45፡ 18-19)
እውነታው ታዲያ ምንድን ነው?
እባክዎን ያሳለፍነውን አንቀፅ ደጋግመው አንብበው እስኪ ትንሽ ያጢኑት!
አሁን ቀጥታ በመጽሃፍ ቅዱስ እና በቁርኣን ውስጥ ያለውን እውነተኛ አንድ አምላክ በተመለከተ እውነታውን የመፈለግ ጉዞውን እንጀምር። በዚህ ጉዞ መጨረሻ ላይ ይህንን አጭር ፅሁፍ በተለይም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ጥቅሶች በቅንነትና በማመዛዘን ካነበቡ በኃላ የእርስዎን ምላሽ ወይም አስተያየት ማወቅ እፈልጋለሁ።
ፍሰቱን ከመጠበቅና በትኩረት እንዲጠና ከሚል ሃሳብ አኳያ እና እርሶም ያለምንም ቅድመ እሳቤ ለማንበብ እንዲመቾት ጥቅሶቹን ያለምንም ተጨማሪ አስተያየት እንዳሉ አቀርባቸዋለሁ፤
ብቸኛው ትክክለኛ አንዱ አምላክ በመፅሀፍ ቅዱስ (ብሉይ ኪዳን):
እስራኤል ሆይ፥ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው
(ኦሪት ዘዳግም 6 : 4)
አንዱ እግዚአብሔር አልሰራችሁምን? በሥጋም በመንፈስም የእርሱ ናችሁ። (NIV English version)
(ሚልኪያ 2 : 15)
ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም። እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።
(ኢሳይያስ 43: 10‐11)
እኔ ፊተኛ ነኝ፥ እኔም ኋለኛ ነኝ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። እንደ እኔ ያለ ማን ነው?
(ኢሳይያስ 44: 6)
እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም እኔ ጻድቅ አምላክና መድኀኒት ነኝ፥ ከእኔም በቀር ማንም የለም።
(ኢሳይያስ 45: 21)
እነዚህን የመሰሉ ሌሎች አንቀፆችንም አስታወሱ?
ብቸኛው ትክክለኛ አንዱ አምላክ በመፅሀፍ ቅዱስ (አዲስ ኪዳን):
እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት።
(ዮሐንስ ወንጌል 17: 3)
ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ
(ማቴዎስ 4: 10)
እስራኤል ሆይ፥ስማ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥…አምላክ አንድ ነው፥ ከርሱም በቀር ሌላ የለም።
(ማርቆስ 12: 29‐32)
አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
(ወደ ጢሞቲዎስ 2: 5)
እነሆም፥አንድ ሰው ቀርቦ፦ቸር መምህር ሆይ፥ የዘለዓለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ አለው። እርሱም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም። (KJV ማቴዎስ 19: 16‐17)
አምላክ (ስላሴ ሳይሆን) አንድ ብቻ መሆኑን የሚያፀኑ ሌሎች አንቀፆችንም ማስታወስ ትችላለህ?
ብቸኛው ትክክለኛ አንዱ አምላክ በቁርአን
(( قل هو الله أحد . الله الصمد . لم يلد ولم يولد . ولم يكن له كفواً أحد)). በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ . አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ . አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ . ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡»
(ሱራ ቁጥር 112: አንቀፅ 1‐4)
(( لا إله إلا أنا فاعبدون )) . ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ
(ምዕራፍ ቁጥር 21: አንቀፅ 25)
(( لقد كفر الذين قالوا إن الله ثالث ثلاثة وما من إله إلا إله واحد وإن لم ينتهوا عما يقولون ليمسن الذين كفروا منهم عذاب أليم )). እነዚያ «አላህ የሦስት ሦስተኛ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ ከአምላክም አንድ አምላክ እንጅ ሌላ የለም፡፡ ከሚሉትም ነገር ባይከለከሉ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል፡፡
(ምዕራፍ ቁጥር 5: አንቀፅ 73)
(( إن إلهكم لواحد )). አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡
(ምዕራፍ ቁጥር 37: አንቀፅ 4)
(( أإله مع الله قل هاتوا برهانكم إن كنتم صادقين)). ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? «እውነተኞች እንደኾናችሁ፤ አስረጃችሁን አምጡ» በላቸው፡፡(ምዕራፍ ቁጥር 27: አንቀፅ 64)
በእውነቱ ይህችው መልዕክት (የአምላክ አንድነት) የተከበረው ቁርአን መሰረታዊ ጭብጥ ነች።
ማጠቃለያ
እነዚህና ሌሎች በቁርአንና በመፅሀፍ ቅዱስ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ማስረጃዎች ምንም በማያጠራጥር መልኩ አምላክ አንድ ብቻ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው። መፅሀፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል: "እስራኤል ሆይ! ስማ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥… አምላክም አንድ ነው፥ ከርሱም በቀር ሌላ የለም።"(ማርቆስ 12: 29‐32)ይህም በቁርአን እንዲህ ያለውን ያስታውሰናል:(قل هو الله أحد) (በል እርሱ አሏህ አንድ ነው።)(ምዕራፍ ቁጥር 112: አንቀፅ 1)
መፅሀፍ ቅዱስ አምላክ አንድ መሆኑን ብቻ ሳይሆን የሚያረጋግጠው እርሱ ብቻውን ፈጣሪና ብቻውን አዳኝ መሆኑንም ያረጋግጣል።"ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም። እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።"(ኢሳያስ 43: 10‐11)
በዚህም ኢየሱስም ይሁን መንፈስ ቅዱስ አልያም ሌላ አምላክ እንደሆነ መሞገት ምንም የተመረኮዘበት ድጋፍ የሌለው ከንቱ ሙግት መሆኑ ግልፅ ይሆናል። እነርሱ ከአሏህ ፍጡራን መካከል የሆኑ አንዳች ስልጣን የሌላቸው ናቸው። እነርሱም አምላክ አይደሉም፤ አምላክም ለሰው ልጆች የተገለፀም በሰው ላይም የሰረፀ አይደለም። አምሳያም የለውም። መፅሀፍ ቅዱስም ይሁን ቁርአን እንደገለፁት እርሱን የሚመስል አንዳችም የለም።
በጥመታቸውና ከእርሱ ውጭ አምላክ አድርገው በመያዛቸው በአይሁዶች ላይ ተቆጥቷል።"የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ።"(ኦሪት ዘኁልቁ 25: 3)የአሏህ ሰላም ይስፈንበትና ሙሳም ወርቃማ ወይፈናቸውን ሰባብሯል።
በሌላ በኩል ከክርስትያኖች መካከል የሆኑ በአንድ አምላክ ብቻ የሚያምኑ ሰዎችም በአምላክ አንድነት ስላመኑ፣ አንዱን አምላክ ብቻ ከሚሰብከው የዒሳ አስተምህሮ አናፈነግጥም በማለታቸውና የጳውሎስ መጤ የስላሴ አስተምህሮን አንቀበልም በማለታቸው ስቃይና እንግልትም ደርሶባቸዋል።
ንግግራችንን ስንቋጭ አሏህ አደምን፣ ኑሕን፣ ኢብራሂምን፣ ሙሳን፣ ዒሳን፣ ሙሓመድንና ሌሎችም ነቢያትና መልዕክተኞችን (ሶለዋቱሏሂ ወሰላሙሁ ዓለይሂም አጅመዒን) የላካቸው ሰዎችን በአሏህ ወደ ማመን፣ ያለምንም ተጋሪና ብጤ እርሱን በብቸኝነት ወደ ማምለክ ጥሪ እንዲያደርጉ ነው። ብቸኛዋ ተልዕኳቸውም ይህችው ነች:
እውነተኛው አምላክ አንድ ነውና እርሱን ብቻ አምልኩ።
የነቢያቶችና የመልዕክተኞች ተልዕኮ አንድ በመሆኑ ሃይማኖታቸውም አንድ ነው። ታዲያ የነዚህ ነቢያትና ሩሱሎች ሃይማኖት ምንድን ነው?
የተልዕኳቸው ዋነኛ ጭብጥ "ተስሊም" ለአላህ (ትእዛዝ እጅ መስጠት) ላይ የሚሽከረከር ነው። ይህች "ኢስላም" የሚለውን ቃል በዓረብኛ ቋንቋ ያለውንም አረዳድ የምትገልፅ ቃል ነች።
ኢስላም የነቢያቶችና የሩሱሎች ሁሉ ሃይማኖት መሆኑን የተከበረው ቁርአን በአፅንኦት ገልጿል። ይህንን ቁርአናዊ እውነታ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይም መረዳት ይቻላል። (ይህንኑ እውነታ በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ መኖሩን ኢንሻአሏህ በሚቀጥለው መፅሀፋችን እንቃኘዋለን።)
በመጨረሻም መዳንን ለማግኘት ከላይ የተጠቀሰውን መልእክት በፈቃደኝነት እና በሙሉ ልብ መቀበል እና ማመን አለብን። ይሁን እንጂ ይህን ማድረግ ብቻውን በቂ አይደለም! ይልቁንም በሁሉም የአላህ እውነተኛ ነቢያት (ነብዩ መሐመድን ጨምሮ) ማመን እና እውነተኛ መመሪያቸውን እና ትምህርቶቻቸውን መከተል ይጠበቅብናል። የስኬትና የዘላለማዊ ሕይወት መድረሻው ይህ ነው!
ስለሆነም እውነትን በቅንነት የምትፈልግ እና መዳንንም የምትወድ የሆንክ ሆይ! ጊዜው ከማለፉ በፊት አሁኑኑ ይህንን ጉዳይ ማጤን ይችላሉ! ድንገት የሚመጣው ሞት ሳይቀድሞ በፊት! መቼ እንደሆነ ማን ያውቃል?
ይህንን አሳሳቢ ጉዳይ በአስተዋይ አእምሮና በታማኝ ልብ በጥልቅ ካሰቡበትና ከተረዱት በኋላ አምላክ ተጋሪ የሌለው አንድና ልጅም የሌለው መሆኑን ማረጋገጥና በእርሱ ማመን እርሱን ብቻም ማምለክና፤ ሙሓመድም እንደነ ኑሕ፣ ኢብራሂም ሙሳ እና ዒሳ የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን ማመን ይችላሉ።
አሁን ‐ከፈለጉ‐ እንዲህ በማለት እነዚህን ቃላት መናገር ነው የሚጠበቅብዎ:‐
"አሽሀዱ አን ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአነ ሙሓመደን ረሱሉሏህ" (ትርጉሙም: ከአሏህ በቀር በእውነት ሊያመልኩት የሚገባ አምላክ እንደሌለ ሙሓመድም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ።)
ይህ የምስክርነት ቃል በዘላለማዊው ህይወት ጎዳና ላይ የመጀመሪያው እርምጃ እና የጀነት በርም ትክክለኛዋ ቁልፍ ነች።
ይህንኑ ጎዳና ሊጓዙበት ከወሰኑ የሙስሊም ጓደኛዎን፣ ወይም ጎረቤትዎን ወይም በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የእስልምና ማዕከል፣ ወይም እኔን ማነጋገር ይችላሉ። (እርሶን መርዳቴ እድለኝነት ነው)።
( قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَى أَنْفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِنْ رَحْمَةِ اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ وَأَنِيبُوا إِلَى رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا لَهُ مِنْ قَبْلِ أَنْ يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنْصَرُونَ وَاتَّبِعُوا أَحْسَنَ مَا أُنْزِلَ إِلَيْكُمْ مِنْ رَبِّكُمْ مِنْ قَبْلِ أَنْ يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ بَغْتَةً وَأَنْتُمْ لَا تَشْعُرُونَ ) በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡ ቅጣቱም ወደእናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትርረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ (በመጸጸት) ተመለሱ፡፡ ለእርሱም ታዘዙ፡፡ እናንተ የማታውቁ ስትኾኑም ቅጣቱ በድንገት ሳይመጣባችሁ በፊት ከጌታችሁ ወደናንተ የተወረደውን መልካሙን (መጽሐፍ) ተከተሉ፡፡»የተከበረው ቁርአን ‐ ምዕራፍ ቁጥር 39: አንቀፅ ቁጥር 53 ‐ 55
አንድ ተጨማሪ ጉዳይ…
ማሳረጊያ ሃሳብ:
ይህችን መልዕክት እውነትን ፍለጋ በቅንነት ካነበቡ በኃላ ትክክለኛ እውነትን ፈላጊዎች እንዲህ ሊጠይቁ ይችላሉ: "እውነታው ምንድን ነው? ስህተቱስ? ምንስ ይጠበቅብናል?"
እነዚህንና መሰል ሃሳቦችን ኢንሻአሏህ በሚቀጥለው መፅሀፌ አብራራቸዋለሁ።
ለተጨማሪ መረጃ፣ ወይም ጥያቄም ይሁን አስተያየት ፀሀፊውን በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ:
ሳ. ቁ. 418 ‐አል‐ሁፉፍ ‐ አል‐አሕሳእ 31982 በሳዑዲ ዓረቢያ ግዛትabctruth@hotmail.com / info@abctruth.net
አልያም ቢሮ…………